1
ምስጋና የዓለማ ጌታ ለሆነው አላህ ይሁን፤ በተከበሩ በሆኑት መልእክተኛው፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ባጠቃላይ የአላህ ሰላም እና እዝነት ይስፈን፡፡ ይህ በይዘት አነስ ያለ መጽሐፍ በውስጡ (አላህን (ሱ.ወ) ለማወደስ የሚረዱ ቃላትን፣ ከቁርአን የተወሰዱ ዱዓዎችን፣ ከነቢዩ ሐዲሶች የተወሰዱ ዱዓዎችን፣ ከሰይጣን እና መሰል መጥፎ ነገሮች መጠበቂያ የሆኑ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተዘገቡ መጠበቂያ ዱዓዎቸን፣ ለመንፈሳዊ ሕክምና የሚያገለግሉ ሸሪዐዊ መሰረት ያላቸው ዱዎችን፣ የቀን እና የማታ አዝካሮችን) እና የዱዓ ሥነ-ሥርአቶችን አካቶ የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሙስሊም በቁርአን እና በሐዲስ ውስጥ በሰፈሩት ዱዓዎች ታግዞ ዱዓ በማድረግ ላይ የራሱን ትግል እንዲያደርግ በማሰብ እንዲሁም በርካታ መልካም ነገሮችን ሰብሰበው የያዙ ዱዓዎችን በተቻለኝ አቅም ትክክለኛ ከሆኑ ሐዲሶች ብቻ በመሰብሰብ በመጽሐፉ ውስጥ ለማስፈር ብርቱ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ እነዚህ ዱዓዎች በዐረቢኛ ቋንቋ የተጻፉ ከመሆናቸው በተጨማሪ ትርጉማቸውና አነባበባቸው እንዲሁ አንድ ላይ በትይዩ ሰፍሯል፡፡
አዘጋጁ
ዶ/ር ዐብደላህ ኢብን ሐሙድ አል-ፉረይሕ