1
أَعُوذُ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ١
﴿الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ ٢ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ٣ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ ٤ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ ٥ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ ٦ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ ٧﴾
7 ጊዜ የአል-ፋቲሐን ምዕራፍ ማንበብ
/ከተረገመው ሸይጣን በአላህ እጠበቃለሁ፡፡
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩሕሩሕ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
1- ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፡፡
2- እጅግ በጣም ሩሕሩሕ በጣም አዛኝ፡፡
3- የፍርዱ ቀን ባለቤት
4- አንተን ብቻ እንገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን፡፡
5- ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡
6- በእነዚያ በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡ ኣሚን፡፡