1

ሙስሊሞች ሆይ! ሁላችሁም ምንጊዜም ከአላህ (ሱ.ወ) ፈላጊ የሆናችሁ ድኾች ናችሁ፡፡ በርሱ ላይ ከሚነገሩ ያልተገቡ ነገሮች ሁሉ በእጅጉ የጠራው አላህ (ሱ.ወ) ፍላጎቶቻችሁን በማሟላት ረገድ የተብቃቃ የሆነ ጌታ ነው፡፡እነዚህ ፍላጎቶቻችሁን ሊያሳኩላችሁ የሚችሉ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በትክክለል ከተዘገቡ ሐዲሶች የተውጣጡ ዱዓዎች እነሆ ቀርበውላችኋልና ልቦናዎቻችሁን አዘጋጁላቸው፡፡ ዱዓዎቹ ሁሉንም መልካም ነገሮች አጠቃለው የያዙ በመሆናቸው በቻላችሁት አቅም በቃላችሁ ለማጥናት ሞክሩ፡፡ ዱዓዎቹ የምትፈልጓቸውን ጉዳዮች በውስጣቸው ቀላልና ትንሽ በሆኑ ቃላት አጠቃለው የያዙ በትርጉም ረገድ ደግሞ ሰፋፊ ትርጓሜዎች ያዘሉ ናቸው፡፡ ከእናንተ የሚፈለገው ልቦናዎቻችሁን በወጉ ማዘጋጀትና ለጌታችሁ እጅግ መተናነስ ነው፡፡

1/1