3
- አላህ ሆይ! እኔ ከሰራሁት ክፋት እና ካልሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ ነብዩ ብዙ ጊዜ የሚያደርጉት ዱዓ ነው፡፡
- “አለህ ሆይ እያወቁም ሆነ ሳላውቅ ከአንተ ጋር እንዳላሻርክ በአንተ እጠበቃለሁ ፣ ለማላውቀው ነገር ይቅርታን እለምናለሁ” (ግብዝነትን የሚያስወግድ ዱዓ ነው)
- “አለህ ሆይ ፣ ጸጋህን ከማጣት ፣ በጤንነት ላይ ለውጥ ፣ ከቅጣትህ ድንገተኛ እና ከቁጣህ ሁሉ በአንተ እጠበቃለሁ።”
- “አለህ ሆይ ፣ ከሚጸየፉ ሥነ ምግባሮች እና ድርጊቶች ፣ ሁሉ፣ከባዶ ምኞቶችና በሽታ በአንተ እጠበቃለሁ”
- አላህ ሆይ! ከመከራ እና ስቃይ፤ ከጉስቁልና፤ከመጥፎ ፍርድ፤ ከጠላቶች መደሰት፤ በአንተ እጠበቃለሁ፡
- አላህ ሆይ ከአካለ ስንኩልነት ፣ ከስንፍና ፣ ከፈሪነት ፣ ከስስታምነት ፣ ከመጃጀት ፣ እንዲሁም ከመቃብር ሥቃይ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ አላህ ሆይ ለራሴ ፍራቻ...
- አለህ ሆይ! ከሀዘንና ትካዜ፤ ከደካማነትና ስንፍና፤ ከስህተትና ፍርሃት ከእዳ ጫናና ከሽንፈት በአንተ እጠበቃለሁ፤
- “አለህ ሆይ ፣ ከጆሮዬ ክፋት ፣ ከእይታዬ ክፋት ፣ ከምላስም ክፋት እና ከልቤ ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ
- «አላህ ሆይ ከእሳት ፈተና እና ከእሳት ስቃይ ፤ ከመቃብር ፈተና ፤ከመቃብር ሥቃይ፤ ከሀብት ፈተና ፣ ከድህነት ከመሲሂደጃል ፈተና በአንተ እጠብቅሃለሁ »
- “አለህ ሆይ በአንተ ኃያልነት እጠበቃለሁ ፣ እንዳልሳሳት ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አይሞትም ፣ የማይሞት ህያው እና ታዳጊ ነህ”
- “አለህ ሆይ ፣ ከለምጽ ፣ ከእብደት ፣ ከቁምጥና እና ከክፉ በሽታዎች በአንተ እጠበቃለሁ ፡፡”
- “አለህ ሆይ! ከመጥፎ ቀን ፣ ከመጥፎ ምሽት ፣ ከክፉ ሰዓት ፤ ከመጥፎ ሌሊት፤ ከመጥፎ ቋሚ ጎሮቤት በአንተ እጠበቃለሁ”
- ከሚታየው እና ከተሰወረው ፈተና በአለህ እጠበቃለሁ፡፡