7

«اللَّهُمَّ إِنِّي عَبْدُكَ ابْنُ عَبْدِكَ ابْنُ أَمَتِكَ نَاصِيَتِي بِيَدِكَ مَاضٍ فِيَّ حُكْمُكَ عَدْلٌ فِيَّ قَضَاؤُكَ، أَسْأَلُكَ بِكُلِّ اسْمٍ هُوَ لَكَ سَمَّيْتَ بِهِ نَفْسَكَ أَوْ أَنْزَلْتَهُ فِي كِتَابِكَ أَوْ عَلَّمْتَهُ أَحَدًا مِنْ خَلْقِكَ أَوِ اسْتَأْثَرْتَ بِهِ فِي عِلْمِ الْغَيْبِ عِنْدَكَ أَنْ تَجْعَلَ الْقُرْآنَ رَبِيعَ قَلْبِي وَنُورَ صَدْري وَجِلَاءَ حُزْنِي وَذَهَابَ هَمِّي»
{وهو دعاء الهم والحزن}

‹‹አልላሁምመ ኢንኒ ዐብዱከ ኢብኑ ዐብዲከ ኢብኑ አመቲከ ናሲየቲ ቢየዲክ ማዲን ፊ ሑክሙክ ዐድሉን ፊ ቀዷኡክ አስአሉከ ቢኩልሊ-ስሚን ሁወ ለክ ሰምመይተ ቢሂ ነፍሰክ አው አንዘልተሁ ፊ ኪታቢክ አው ዐልለምተሁ አሐደን ሚን ኸልቂክ አዊ-ስተእሠርተ ቢሂ ፊ ዒልሚ-ልገይቢ ዒንደክ አን ተጅዐለል ቁርአነ ረቢዐ ቀልቢ ወኑረ በሰሪ ወጀላአ ሑዝኒ በዘሃበ ሀምሚ፡፡››

/አላህ ሆይ! እኔ ባሪያህ፣ የወንድ ባሪያህና የእንስት ባሪያህ ልጅ ነኝ፡፡ የሁሉ ነገሬ መነሻ በእጅህ ነው፡፡ ውሳኔህ በኔ ላይ ተፈጻሚ ነው፡፡ ብይንህ በኔ ላይ ፍትሐዊ ነው፡፡ ያንተ በሆኑትና አንተ ራስህን በሰየምክባቸው ወይም በመጽሐፍህ -(በቁርአን ውስጥ-) ባወረድካቸው ወይም ከፍጡራንህ መካከል ለአንዱ ባሳውቅካቸው ወይም አንተ ዘንድ ባለው የሩቅ ክስተቶች እውቀት ውስጥ ውስጥ በልዩ ሁኔታ ባስቀመጥካቸው ስሞች ሁሉ ቁርኣንን የልቤ መርጊያ፣ የልቦናዬ ብርሃን፣ የሐዘኔ መገላገያና የጭንቀቴ ማስወገጃ ታደርግልኝ ዘንድ እጠይቅሃለሁ፡፡/

(ይህ ዱዓ የጭንቅና የሐዘን ዱዓ ነው፡፡)

7/19