«اللهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنَ الْخَيْرِ كُلِّهِ عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ، مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ الشَّرِّ كُلِّهِ، عَاجِلِهِ وَآَجِلِهِ مَا عَلِمْتُ مِنْهُ، وَمَا لَمْ أَعْلَمْ، اللهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنْ خَيْرِ مَا سَأَلَكَ عَبْدُكَ وَنَبِيُّكَ مُحَمَّدٌ (صلی الله علیه وسلم)، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا عَاذَ مِنْهُ عَبْدُكَ وَنَبِيُّكَ، اللهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْجَنَّةَ وَمَا قَرَّبَ إِلَيْهَا مِنْ قَوْلٍ أَوْ عَمَلٍ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ النَّارِ وَمَا قَرَّبَ إِلَيْهَا مِنْ قَوْلٍ أَوْ عَمَلٍ، وَأَسْأَلُكَ أَنْ تَجْعَلَ كُلَّ قَضَاءٍ تَقْضِيهِ لِي خَيْرًا»
{وهو من جوامع الدعاء وكوامله}
‹‹አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ሚነ-ኸይሪ ኩልሊሂ ዓጂሊሂ ወኣጂሊሂ ማ ዐሊምቱ ሚንሁ ወማ ለም አዕለም ወአዑዙ ቢከ ሚነ-ሽሸርሪ ኩልሊሂ ዓጂሊሂ ወኣጂሊሂ ማ ዐሊምቱ ሚንሁ ወማ ለም አዕለም አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ሚኒ ኸይሪ ማ ሰአለከ ዐብዱከ ወነቢይዩከ ሙሐምመዱን ሰልለ-ላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ ማ ዓዘ ቢከ ዐብዱከ ወነቢይዩክ አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ-ልጀንነተ ወማ ቀርረበ ኢለይሃ ሚን ቀውሊን አቀው ዐመል ወአዑዙ ቢከ ሚነ-ንናር ወማ ቀርረበ ኢለይሃ ሚን ቀውሊን አው ዐመል ወአስአሉከ አን ተጅዐለ ኩልለ ቀዳኢን ተቅዲሂ ሊ ኸይራ፡፡››
/አላህ ሆይ! ከመልካም ነገሮች መካከል የቀደመውንም የዘገየውንም መልካሙን ሁሉ እጠይቅሃለሁ፡፡ ከመጥፎ ነገሮች የቀደመውንም የዘገየውንም መጥፎ ነገር ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! ባሪያህና ነቢይህ የሆኑት ሙሐመድ የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን የጠየቁህን መልካም ነገሮች ሁሉ እጠይቅሃለሁ፡፡ ባሪያህና ነቢይህ የሆኑት ሙሐመድ የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን ከተጠበቁብህ መጥፎ ነገሮች ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! ጀነትን እጠይቅሃለሁ፡፡ ከንግግር ወይም ከስራ ወደርሷ የሚያቃርበውን እጠይቅሃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! ከእሳት ቅጣት በባንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከንግግርም ወይም ከስራ ወደርሷ ከሚያቃርብ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! በእኔ ላ የምትወስናቸው ውሳኔዎች በሙሉ መልካም ውሳኔዎች እንድታደርጋቸው እጠይቅሃለሁ፡፡/
(ይህ ዱዓ ሁሉን አጠቃላይና ሁሉንም የሚያሟሉ ከሆኑ ዱዓዎች መካከል አንዱ ነው፡፡