«اللَّهُمَّ بِعِلْمِكَ الْغَيْبَ، وَقُدْرَتِكَ عَلَى الْخَلْقِ، أَحْيِنِي مَا عَلِمْتَ الْحَيَاةَ خَيْرًا لِي، وَتَوَفَّنِي إِذَا عَلِمْتَ الْوَفَاةَ خَيْرًا لِي، وَأَسْأَلُكَ خَشْيَتَكَ فِي الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ، وَكَلِمَةَ الْإِخْلَاصِ فِي الرِّضَا وَالْغَضَبِ، وَأَسْأَلُكَ نَعِيمًا لَا يَنْفَدُ، وَقُرَّةَ عَيْنٍ لَا تَنْقَطِعُ، وَأَسْأَلُكَ الرِّضَاءَ بِالْقَضَاءِ، وَبَرْدَ الْعَيْشِ بَعْدَ الْمَوْتِ، وَلَذَّةَ النَّظَرِ إِلَى وَجْهِكَ، وَالشَّوْقَ إِلَى لِقَائِكَ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ ضَرَّاءَ مُضِرَّةٍ، وَفِتْنَةٍ مُضِلَّةٍ، اللَّهُمَّ زَيِّنَّا بِزِينَةِ الْإِيمَانِ، وَاجْعَلْنَا هُدَاةً مُهْتَدِينَ»
‹‹አልላሁምመ ቢዒልሚከ-ልገይብ ወቁድረቲከ ዐለ-ልኸልቅ አሕዪኒ ማ ዐሊምተ-ልሐያተ ኸይረን ሊ ወተወፍፈኒ ኢዛ ዐሊምተ-ልወፋተ ኸይረን ሊ አስአሉከ ኸሽየተከ ፊ-ልገይቢ ወ-ሽሸሃደህ ወከሊመተ-ልኢኽላሲ ፊ-ርሪዷ ወ-ልገደብ ወአስአሉከ ነዒመን ላ የኝፈድ ወቁርረተ-ልዐይኒ ላ ተንቀጢዕ ወአስአሉከ-ርሪዷ ቢ-ልቀዳእ ወበርደ-ልዕሺ በዕደ-ልመውት ለዝዘተ-ንነዘሪ ኢላ ወጅሂክ ወሽሸውቀ ኢላ ሊቃኢክ ወአዑዙ ቢከ ደርራኢን ሙድርረህ ወፊትነቲን ሙዲልለህ አልላሁምመ ዘይዪና ቢዚነቲ-ልኢማን ወጅዐልና ሁዳተን ሙህተዲን፡፡››
/አላህ ሆይ! ስውር የሆነውን በሚያውቀው እውቀትህ፣ በፍጡራንህ ላይ ባለህ ችሎታ ሕይወት ለኔ መልካም መሆኗን ካወቅክ በሕይወት አቆየኝ፡፡ መሞቴም ለኔ መልካም መሆኑን ካወቅክ ግደለኝ፡፡ በምስጢርም በይፋም አንተን መፍራትን፣ በደስታና በንዴት ጊዜ ቅን ንግግርን እጠይቅሃለሁ፡፡ የማያልቅ ጸጋን፣ የማይቋረጥ የአይን ማረፊያን፣ ውሳኔህን ወደዶ መቀበልን፣ ከሞት በኋላ የተድላ ሕይወትን፣ ወደ ፊትህ መመልከት የሚሰጠውን እርካታን፣ አንተን የመገናኘትን ናፍቆት እጠይቅሃለሁ፡፡ ጉዳትን ከሚያመጡ ጎጂ ነገሮች፣ ቅኑን መንገድ ከሚያስት ፈተና ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! በኢማን ጌጥ አጊጠን፡፡ ቀጥተኛውን መንገድ ተመርተው ሌሎችን ወደቀጥተኛው መንገድ የሚመሩ አድርገን፡፡/