«اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ فِعْلَ الخَيْرَاتِ، وَتَرْكَ الْمُنْكَرَاتِ، وَحُبَّ الْمَسَاكِينِ، وَأَنْ تَغْفِرَ لِي وَتَرْحَمَنِي، وَإِذَا أَرَدْتَ فِتْنَةً فِي قَوْمٍ فَتَوَفَّنِي غَيْرَ مَفْتُونٍ، وَأَسْأَلُكَ حُبَّكَ وَحُبَّ مَنْ يُحِبُّكَ، وَحُبَّ عَمَلٍ يُقَرِّبُ إِلَى حُبِّكَ»
{قال صلى الله عليه وسلم عن هذه الدعوات: إِنَّهَا حَقٌّ فَادْرُسُوهَا ثُمَّ تَعَلَّمُوهَا}
‹‹አልላሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ፊዕለ-ልኸይራት ወተርከ-ልሙንከራት ወሑብበ-ልመሳኪን ወአን ተግፊር ሊ ወተርሐምኒ ኢዛ አረድተ ፊትነተን ፊ ቀውሚን ፈተወፍፈኒ ገይረ መፍቱን ወአስአሉከ ሑብበክ ወሑብበ መን ዩሒብቡክ ወሑብበ ዐመሊን ዩቀርሪቡ ኢላ ሑብቢክ፡፡››
/አላህ ሆይ! መልካም ነገሮችን መተግበርን፣ መጥፎ ነገሮችን መተውን፣ ችግረኛ ሰዎችን መውደድን፣ ወንጀሎቼን እንድትምርልኝ፣ እንድታዝንልኝ፣ በሕዝቦች መካከል ፈተናን የሻትክ ከሆንክ የተፈተንኩ ሳልሆን እንድትገድለኝ እጠይቅሃለሁ፡፡ ውዴታህን፣ የሚወዱህን ባሮች መውደድንና ወደ ውዴታህ የሚያቃርቡ ስራዎችን መውደድን እጠይቅሃለሁ፡፡/
(እነዚህን ዱዓዎች አስመልክተው ነቢዩ የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹በርግጥ እነርሱ አውነተኛ ናቸው፡፡ እውቋቸው ከዚያም ተማሯቸው፡፡)