3

«وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا، وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ، إِنَّ صَلَاتِي، وَنُسُكِي، وَمَحْيَايَ، وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ، لَا شَرِيكَ لَهُ، وَبِذَلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا مِنَ الْمُسْلِمِينَ، اللهُمَّ أَنْتَ الْمَلِكُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، أَنْتَ رَبِّي، وَأَنَا عَبْدُكَ، ظَلَمْتُ نَفْسِي، وَاعْتَرَفْتُ بِذَنْبِي، فَاغْفِرْ لِي ذُنُوبِي جَمِيعًا، إِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ، وَاهْدِنِي لِأَحْسَنِ الْأَخْلَاقِ لَا يَهْدِي لِأَحْسَنِهَا إِلَّا أَنْتَ، وَاصْرِفْ عَنِّي سَيِّئَهَا لَا يَصْرِفُ عَنِّي سَيِّئَهَا إِلَّا أَنْتَ، لَبَّيْكَ وَسَعْدَيْكَ وَالْخَيْرُ كُلُّهُ فِي يَدَيْكَ، وَالشَّرُّ لَيْسَ إِلَيْكَ، أَنَا بِكَ وَإِلَيْكَ، تَبَارَكْتَ وَتَعَالَيْتَ، أَسْتَغْفِرُكَ وَأَتُوبُ إِلَيْكَ»
{وهو من أدعية استفتاح الصلاة، خاصة في صلاة قيام الليل}

ወጀህቱ ወጅሂየ ልለዚ ፈጠረ ሰማዋቲ ወል አርደ ሀኒፈን ወማ ካነ ሚነል ሙሽርኪን ኢነ ሶላቲ ወኑሱኪ ወመህያየ ወመማቲ ሊላሂ ረቢል ኣለሚን ላሸሪከ ለሁ ወቢዛሊከ ኡሚርቱ ወ አነ ሚነል ሙስልሚን አላሁመ አንተል መሊኩ ላኢላሀ ኢላ አንተ አንተ ረቢ ወ አነ አብዱከ ዘለምቱ ነፍሲ ወእተረፍቱ ብዘንቢ ፈግፊርሊ ዙኑቢ ጀሚአን ኢነሁ ለየግፊሩዙኑበ ኢላ አንተ.

ቀጥ በማለት ወደዚያ ሰማያትንና ምድርን ወደ ፈጠረው አምላክ ፊቴን አዞርኩ ፤እኔ ከአጋሪዎች አይደለሁም ስግደቴም፤ መስዋዕቴም፤ህይወቴም፤ሞቴም አጋር ላሌለው ለአለማት ጌታ ለአለህ ነው፡፡ ይህን እንድፈፅም ታዝዣለው፤እኔ ከሙስሊሞች ነኝ፤ አለህ ሆይ ንጉሱ አንተ ነህ፤ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፤አንተ ጌታዬ ነህ፤ እኔ ደግሞ ባሪያ ነኝ፤ እራሴን በድያለው፤ ሀጢያት መስራቴን አውቃለው፤ ሁሉንም ሐጢአቶቼን ማርልኝ፤ ከአንተ ውጭ ሐጢኣቶችን የሚምር የለም፤ መልካም ስነ-ምግባርን መጎናፀፍ አብቃኝ፤ ለመልካም ስነ-ምግባር የምታበቃው አንተ ብቻ ነህና፤ አለህ ሆይ መልካም ነገሮች ሁሉ በእጅህ ናቸው፤ ክፉ ነገሮች ከአንተ የሚመነጩ አይደሉም፤ እኔ (የተገኘሁት) በአንተ ነው፡፡ ወደ አንተም እመለሳለው፤የተቀደስክ ልዑልም ነህ፤ ምህረትህን እለምናለው፤ ወደ አንተ በፀሎት እመለሳለው፡፡

(በተለይም በምሽት ሶላት ወቅት ሶላቱን ከሚከፍቱ ዱዓ አንዱ ነው)

3/16