«اللهُمَّ رَبَّ جَبْرَائِيلَ، وَمِيكَائِيلَ، وَإِسْرَافِيلَ، فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ، عَالِمَ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ، أَنْتَ تَحْكُمُ بَيْنَ عِبَادِكَ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ، اهْدِنِي لِمَا اخْتُلِفَ فِيهِ مِنَ الْحَقِّ بِإِذْنِكَ، إِنَّكَ تَهْدِي مَنْ تَشَاءُ إِلَى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ»
{وهو من أدعية استفتاح الصلاة، خاصة في صلاة قيام الليل}
{ويقال عند التباس الحق وورود الشبهة على القلب}
‹‹አልላሁምመ ረብበ ጀብራኢል ወሚካኢል ወኢስራፊል ፋጢረ-ስሰማዋቲ ወ-ልአርዲ ዓሊመ-ልገይቢ ወ-ሽሸሃደቲ አንተ ተሕኩሙ ብይነ ዒባዲከ ፊ ማ ካኑ የኽተሊፉን ኢህዲኒ ሊማ-ኽቱሊፈ ፊሂ ሚነ-ልሐቅቂ ቢኢዝኒክ ኢንነከ ተህዲ መን ተሻኡ ኢላ ሲራጢን ሚስተቂም፡፡››
/የጂብሪል፣ የሚካኢል፣ የኢስራፊል ጌታ የሆንከው፣ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ የሆንከው፣ ሩቁንም እውነታውንም ዐዋቂ የሆንከው አላህ ሆይ! ባሮችህ ይለያዩበት በነበረው ጉዳይ በመካከላቸው ፈራጅ ነህ፡፡ ከተለያዩበት ጉዳይ መካከል ወደትክክለኛው መንገድ ምራኝ፡፡ በርግጥ አንተ የምትሻውን ወደቀጥተኛው መንገድ የምትመራ -(ጌታ)- ነህ፡፡/
(ይህ ዱዓ በተለይ የሌሊት ሰላት መክፈቻ የሆነ ዱዓ ነው፡፡)
(በሌላ በኩል እውነተኛ በሆነ ጉዳይ ላይ ውዥንብር ሲፈጠር እና በልቦና ውስጥ የእውነትና ሐሰት መደበላለቅ ሲፈጠር የሚደረግ ዱዓ ነው፡፡)