5

አምስተኛ፡- ዱዓ የሚያደርግ ሰው ምግቡም ሆነ መጠጡ በሐራም (ፍጹም ክልክል በሆነ መንገድ) የተገኘ መሆን የለበትም፡፡ ምክንያቱም በሐራም መንገድ የተገኘ ምግብ እና መጠጥ በአላህ (ሱ.ወ) ዱዓ ምላሽን ከሚያስከለክሉ ነገሮች መካከል ይመደባሉ፡፡ ይህን አስመልከተው አቡ ሁረይራህ (ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፤ “አንድ መንገድ የሚያረዝም፣ ፀጉሩ የተዘበራረቀ፣ መልኩ የተለወጠ የሆነ ሰው ምግቡ በሐራም መንገድ የተገኘ፣ መጠጡም በሐራም መንገድ የተገኘ አንዲሁም ልብሱ በሐራም መንገድ የተገኘ፣ ሐራም ነገር የተመገበ ሆኖ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ‹‹ጌታዬ ሆይ! ጌታዬ ሆይ!›› ቢል ለዚህ አይነቱ ሰው እንዴት ምላሽ ሊሰጠው ይችላል?” (ሙስሊም በሐዲስ ዘገባ ቁጥር 1015 ላይ ዘግበውታል)

5/16