4
አራተኛ፡- ማንኛውም ሙስሊም በፈጸማቸው ወንጀሎች ምክንያት ከአላህ (ሱ.ወ) የራቀ ቢሆንም በፈጸማቸው ወንጀሎች ተጸጽቶ ንሰሐ (ተውባህ) በማድረግ ወደአላህ (ሱ.ወ) ከተመለሰ አላህ (ሱ.ወ) በባሮቹ ንሰሐ (ተውባህ) እጅግ እንደሚደሰት ሊያውቅ ይገባል፡፡ በአንጻሩ በወንጀሎቹ ምክንያት አላህ (ሱ.ወ) ለዱዓዎቼ ምላሽ አይሰጠኝም የሚል ሃሳብ በልቡ ውስጥ ልብ ሊል፣ ከአላህ (ሱ.ወ) እዝነትም ተስፋ ሊቆርጥ አይገባውም፡፡ እንዲያውም ከወንጀሎቹ ተጸጽቶ በንስሐ (ተውባህ) ወደ አላህ (ሱ.ወ) በመመለሱ ሳቢያ እጅግ ሊደሰትና አላህ (ሰ.ወ)፤ “ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡” (አል-በቀራህ ፡ 186) እንዳለ በልቦናው ውስጥ ሊያሰገባ ይገባል፡፡