1

አንደኛ፡- ዱዓ የሚያደርግ ሰው ዱዓውን በቅንነት ለአላህ (ሱ.ወ) ብቻ የማድረግ፣ ለዱዓው ምላሽ ሊሰጠው የሚችለው አላህ (ሱ.ወ) ብቻ እንደሆነ በልቦናው በጽኑ የማመን ግዴታ አለበት፡፡ ስለሆነም ከአላህ (ሱ.ወ) በስተቀር ማንንም መጠየቅና በዱዓው ውስጥ ነቢይን ወይም መልካም የአላህ ወዳጅን ወይም መልአክን ወይም መልካም የአላህ ባሪያን ወይም ምንም አይነት ፍጡር አማላጅ ማድረግ የለበትም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፤ “አላህንም...ለእርሱ አጥሪዎች ኾናችሁ ተገዙት፡፡” (ጋፊር ፡ 14)

1/16