12

መንፈሳዊ ሕክምና በሚደረግበት ጊዜ መሟላት ያለባቸው ቅድመ-መስፍርቶች ያሉ ሲሆን እነዚህን ቅድመ-መስፈርቶች መጠበቅ (መሟላት) ይኖባቸዋል፡፡

1. ትክክኛው መንፈሳዊ ሕክምና ከቁርአንና ከነቢያዊ ፈለጎች የተወሰዱ፣ በአፈጻጸማቸው ሂደትም ሆነ በአገላለጻቸው አምልኮትን በአላህ ላይ ከማጋርት ተግባራት፣ በኢስላም ላይ መጥ ሆነው ከተጨመሩ ነገሮች (ቢድዐዎች)፣ ፍጹም ክልክል ከሆኑ ነገሮችና ተግባራት ፍጹም የራቁ ሊሆኑ ይገባል፡፡

2. ማንኛውም ሙስሊም ጌታውን የሙጥኝ ማለትና በእሱም ላይ ብቻ መመካት አለበት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንፈሳዊ ሕክምና ጤናን ለማግኝት አንድ ምክንያት እንጂ ካለ አላህ ፈቃድ ማዳን እንደማይችል ማወቅ አለበት፡፡

3. መንፈሳዊ ሕክምናውን ለሙከራ ብሎ ማድረግ የለበትም፡፡ ይልቁኑ መንፈሳዊ ሕክምናው ሊያመጣው በሚችለው ውጤት የማመን ግዴታ አለበት፡፡ ታማሚውም መንፈሳዊ ሕክምና ሰጪውም መንፈሳዊው ሕክምና በሚያመጣው ውጤትና በመድሃኒትነቱ የማመን ግዴታ አለባቸው፡፡

4. ቁርአን ሁሉም አንቀጾቹ መድሃኒት ናቸው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፤ ‹‹ከቁርአንም ለምእመናን መድኃኒትና እዝነት የኾነን እናወርዳለን፡፡›› (አል-ኢስራእ ፡ 82)

5. ማንኛውም የታመመ ሰው ራሱን በራሱ በመንፈሳዊ ሕክምና ማከሙ የተሻለ ነው፡፡ ይህን ማድረጉ በሕክምናው በጣም እንዲያምንና ምንጊዜም የጌታውን እርዳታ ፋለጊ እንደሆነ ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡ መንፈሳዊው ሕክምና አእምሮን በማጣመርና በቅን ልቦና የሚደረግ ከሆነ አመርቂ ውጤት ይኖረዋል፡፡

12/12