9
9. አላህ (ሱ.ወ) ባሪያው እሱን በማመስገንና በማወደስ ተግባር የተጠመደ መሆኑን በእጅጉ ይወዳልና ይህን በማድረጉ አላህን (ሱ.ወ) በማወደስና በማመስገን እንዳመለከው እንዲቆጠርለት አንድ ሰው የሚያደርገው ዱዓ በውስጡ አላህን (ሱ.ወ) ማመስገንና ማዋደስን አካቶ መያዝ አለበት፡፡ ያለዚያ አላህ (ሱ.ወ) ከባሪያዎቹ የተብቃቃ ጌታ ነው፡፡ በቡኻሪና ሙስሊም ከኢብን መስዑድ (ረ.ዐ) በተዘገበው ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፤ “ከአላህ በስተቀር እንደሱ ሙገሳን የሚወድ የለም ለዚህም ነው አላህ ራሱን ያሞገሰው፡፡”