8
8. ዱዓውን ድምጹን ከፍ ሳያደርግ ዝግ አድርጎ በድብቅ ማድረግ አለበት፡፡ ይህን አስመልክቶ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፤ “ጌታችሁን ተዋርዳችሁ በድብቅም ለምኑት፡፡” (አል-አዕራፍ ፡ 55) ዱዓን ዘግ ባለ ድምጽ በድብቅ ማድረግ አላህን (ሱ.ወ) በቅንነት ወደመለመን በጣም የቀረበ ተግባር ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ነው አላህ (ሱ.ወ) ነቢዩ ዘከሪያን (የአላህ ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን) ያመሰገናቸው፡፡ ይህን አስመልክቶ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፤ “ጌታውን የምስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡” (መርየም ፡ 3)