7
7. ዱዓ የሚያደርግባቸውን ቃላት መደጋገምና ጥያቄውን ለአላህ (ሱ.ወ) በመማጸን አጥብቆ መጠየቅ አለበት፡፡ ኢብን ዐብባስ (ረ.ዐ) ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በበድር ጦርነት እለት ለባልደረቦቻቸው ያደርጉትን ዱዓ እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በእለቱ፤ ‹‹አላህ ሆይ! ቃል የገባህልኝ ፈጽምልኝ፡፡ አላህ ሆይ! ቃል የገባህልኝ ስጠኝ፡፡” በማለት በላያቸው ላይ የነበረው ኩታቸው ከትከሻዎቻቸው ላይ እስኪወድቅ ድረስ ደጋግመው ጌታቸውን ይማጸኑ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ አቢ በክር (ረ.ዐ) ከአጠገባቸው ሳይለዩ፤ ‹‹አንቱ የአላህ ነቢይ ሆይ! ጌታዎን መማጸንዎ ይበቃዎታል፡፡›› ይላቸው ነበር፡፡ ሐዲሱን ሙስሊም በሐዲስ ዘገባ ቁጥር 1763 ዘግበውታል፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ከአቢ ሁረይራህ (ረ.ዐ) በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለደውስ ጎሳ፤ “አላህ ሆይ! የደውስ ጎሳዎችን ቀጥተኛውን መንገድ ምራቸውና ወዲዘህ አምጣቸው፡፡አላህ ሆይ! የደውስ ጎሳዎችን ቀጥተኛውን መንገድ ምራቸውና ወዲዘህ አምጣቸው፡፡” በማለት ደጋግመው ዱዓ አድርገዋል፡፡ ሐዲሰን ቡኻሪ በሐዲስ ዘገባ ቁጥር 2937፣ ሙስሊም በሐዲስ ዘገባ ቁጥር 2524 ዘግበውታል፡፡