6
6. ዱዓ የሚያደርግ ሰው አላህን (ሱ.ወ) በመልካም ስሙ እየጠራ አላህን (ሱ.ወ) መለመን አለበት፡፡ ከዱዓው ጋር የሚስማሙ መልካም ስሞችን በመቀያየር ዱዓ ቢያደርግ የተሻለ ነው፡፡ ለምሳሌ፤ አላህን (ሱ.ወ) ሲሳይ (ሪዝቅ) የሚጠይቅ ከሆነ “ያ ረዝዛቅ /አንተ ሲሳይ ሰጪ የሆንክ ጌታ ሆይ!/”፣ እዝነትን የሚጠይቅ ከሆነ “ያ ረሕማን ያ ረሒም /አንተ እጅግ ሩሕሩሕ እጅግ አዛኝ የሆንከ ጌታ ሆይ!/”፣ ክብርን የሚጠይቅ ከሆነ “ያ ዐዚዝ /አንተ እጅግ የተከበርክ የሆንከ ጌታ ሆይ!/”፣ ምሕረትን የሚጠይቅ ከሆነ “ያ ገፉር /አንተ እጅግ መሐሪ የሆንክ ጌታ ሆይ!/”፣ ከበሽታ መዳንን የሚጠይቅ ከሆነ “ያ ሻፊ /አንተ ከበሽታ አዳኝ የሆንክ ጌታ ሆይ!/” ወ.ዘ.ተ በማለት ከዱዓው ጋር ተያያዥነት ባላቸው መልካም የሆኑ የአላህ (ሱ.ወ) ስሞች ዱዓ ማድረግ አለበት፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፤ “አላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ (ስትጸልዩ) በእርሷም ጥሩት፡፡” (አል-አዕራፍ ፡ 180)