5
5. አንድ ሰው ዱዓ ሲያደርግ በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ኖሮት፣ ዱዓውም ምላሽ እንደሚያገኝ ከልቡ በእርግጠኝነት አምኖ ዱዓ ማድረግ አለበት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዱዓው ቶሎ ምላሽ እንዲያገኝ መቸኮል የለበትም፡፡ በአንጻሩ አላህ (ሱ.ወ) ለዱዓው ምላሽ እንደሚሰጠው ከልቡ በርግጠኛነት ማመን ይኖርበታል፡፡
አቡ ሁረይራህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፤ “በሃጢአት ላይ፣ የዝምድና ግንኙነትን በመቁረጥና ዱዓው ቶሎ ምላሽ እንዲያገኝ እስካልተቻኮለ ድረስ አንድ የአላህ ባሪያ ዱዓው ምላሽ ከማግኘት አይታከተም፡፡” ሲሉ ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ቶሎ መቻኮል ማለት ምን ማለት ነው?›› ተብለው ተጠየቁ፡፡ እሳቸውም፤ “ –(መቻኮል)- ማለት ሰውየው፤ ‹‹በርግጥ ዱዓ አድርጌያለሁ፣ ደጋግሜ አድርጌያለሁ፡፡ ምላሽ ሲሰጠኝ ግን አላየሁም፡፡›› እያለ ተስፋ በመቁረጥ ዱዓ ማድረጉን መተዉ ነው፡፡” በማለት መለሱ፡፡ (ሙስሊም በሐዲስ ዘገባ ቁጥር 2735 ላይ ዘግበውታል)