4

4. ዱዓውን አላህን (ሱ.ወ) በማወደስ እና በመልእክተኛው -(የአላህ ሰላም እና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን)- ላይ ሰለዋት በማውረድ መጀመር አለበት፡፡ ለዚህ ማስረጃ የሚሆነው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረባ የሆኑት ፉዳላህ ኢብን ዑበይድ (ረ.ዐ) አንድ ሰው ሰላት ውስጥ ሆኖ አላህን (ሱ.ወ) ሳያወድስ፣ በአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ላይም ሰለዋት ሳያወርድዱዓ ሲያደርግ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሰሙና፤ “ይህ ሰው እጅግ ተቻኮለ፡፡ ” አሉ፡፡ ከዚያም ሰውየውን ጠርተው፤ “አንዳችሁ ሰላት ሲሰግድ ሰላቱን እጀግ የተከበረውንና የላቀውን አላህን በማመስገን ከዚያም በነቢዩ የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን ሰለዋት ያውርድና ይጀምር፡፡ ከዚያ በኋላ በፈለገው ነገር ዱዓ ያድርግ፡፡” ሲሉ መስማታቸውን አስተላልፈዋል፡፡{[1]}

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ወደፊት በሚጠቀሱትና የቁርአን ምዕራፎች መክፈቻ በሆኑት አላህን (ሱ.ወ) የማመስገኛ ቃላት ከዚያ በነቢዩ የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን ሰለዋት በማውረድና አላህን (ሱ.ወ) በተለያዩ ቃላት በማውደስ ዱዓውን ቢጀምር ለዱዓው ምላሽ ማግኛ መንገዶች በእጅጉ የቀረበ ይሆናል፡፡

4/10