3

3. ሁለት እጆችን ወደላይ ከፍ ማድረግ አለበት፡፡

ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 2 እና 3 ላይ የተመለከቱትን ነቢያዊ ፈለጎችን ዐብደላህ ኢብን ዐብባስ (ረ.ዐ) የሐዲስ ማሰረጃ ነው፡፡ ዐብደላህ ኢብን ዐብባስ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹ዑመር ኢብን አል-ኸጣብ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ ነግረውኛል፡፡ ‹‹የበድር ጦርነት እለት የአላህ መልእክተኛ የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን አምልኮተ-አጋሪያን (ሙሽሪኮች) ብዙ ሺህ እንደሆኑ እንዲሁም ባልደረቦቻቸው ሶስት መቶ አስራ ዘጠኝ እንደሆኑ ተመለከቱ፡፡ ፊታቸውን ወደቂብላህ አቅጣጫ አዙረው እጆቻቸውን ወደላይ ከፍ አድርገው፤ “አላህ ሆይ! ቃል የገባህልኝን እውን አድርግልኝን፡፡ አላህ ሆይ! ቃል የገባህልኝን ስጠኝ፡፡” በማለት ዱዓ አደረጉ፡፡ (ሙስሊም በሐዲስ ዘገባ ቁጥር 1763 ዘግበውታል)

3/10