1

1. ንጹሕ ሆኖ ዱዓ ማድረግ አለበት፡፡ ስለዚህ ለሰላት ዉዱእ እንደሚያደርገው ለዱዓም ዉዱእ ማድረግ አለበት፡፡

ይህን አስመልክተው በቡኻሪና ሙስሊም በተዘገበው ትክክለኛ ሐዲስ አቡ ሙሳ (ረ.ዐ) ከአጎታቸው ከአቢ ዓሚር (ረ.ዐ) ጋር የነበራቸውን ታሪክ አስመልክተው ባስተላለፉት ሐዲስ አጎታቸው አቡ ዓመር (ረ.ዐ) የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ዱዓ እንዲያደርጉላቸው አቡ ሙሳ (ረ.ዐ) ጥያቄውን ለአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲቀርቡላቸው አጥብቀው ጠየቋቸው፡፡ አቡ ሙሳም (ረ.ዐ) አጎታቸው አቡ ዓሚር (ረ.ዐ) በላኳቸው መሰረት ለአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጥያቄውን አቀረቡ፡፡ አቡ ሙሳ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፤ ‹‹የአላህ መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) ውሃ እንዲመጣላቸው አድረገው በመጣላቸው ውሃ ዉዱእ አድርገው የብብታቸውን ንጣት እስከማይ ድረስ እጆቻቸውን ወደላይ ከፍ አድርገው፤ ‹‹አላህ ሆይ! ለአቢ ዓሚር ዑበይድ ወንጀሉን ማርለት፡፡›› በማለት የዱዓ አደረጉ፡፡ አያይዘውም፤ “በትንሳኤ እለት ከበርካታ ፍጡራንህ ወይም ከሰዎች በላይ አድርገው፡፡” ብለው ዱዓ አደረጉ፡፡›› በማለት አስተላልፈዋል፡፡ (ቡኻሪ በሐዲስ ዘገባ ቁጥር 4323፣ ሙስሊም በሐዲስ ዘገባ ቁጥር 2498 ላይ ሐዲሱን ዘግበውታል)

1/10