1

የልመና ቃላትን በመደጋገም ዱዓእ ማድረግ እና አጥብቆ ለመጠየቅ፤

በኢብኑ አባስ ሀዲስ - ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በበድር ዘመቻ ለባልደረቦቻቸው ዱዓእ ባደረጉት ጊዜ እንዲህ ማለታቸው ተነግሯል፡- “ያ አለህ የገባልኝን ቃል ፈጸምልኝ ፡ ያ አለህ የገባልኝን ቃል ስጠኝ” እያለ ይለምናል፡፡ ሽርጡ ከትከሻው እስከሚወድቅ ድረስ አለህን አጥብቆ መለመን አላቆመም ነበር፡፡አቡ በክርም የአለህ ነብይ ሆይ አለህን እንዲ አጥብቆ መለመን ይበቀዎታል” ይላቸዋል፡፡ (ሙሰሊም 1763)

እንደዚሁም በሁለቱ ሳሂህዎች ውስጥ የተጠቀሰው

ከአቡ ሁረይራ ሐዲስ (ረ.ዐ) - ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) - ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእሱ ላይ ይሁንና) እንዲህ አሉ- “ያ አለህ ሆይ ደውስን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ምራ ያ አለህ ሆይ ደውስን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ምራ ፤ አምጣቸውም (ቡካሪ ቁ.2937) (ሙስሊም ቁ. 2524)

1/1